አውደ – ርዕዩ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልከውን የቡና አቅርቦት እንድትጨምር ያግዛል – ቡናና ሻይ ባለሥልጣን
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የሚዘጋጀው አራተኛው ዓለም አቀፍ የገቢ አውደ ርዕይ የኢትዮጵያ ቡና በቻይና የተሻለ ገበያ እንዲኖረው እንደሚያደርግ ተገለጸ።
አውደ ርዕዩ በፈረንጆቹ ከህዳር 5 እስከ 10 ቀን 2021 በሻንጋይ የሚካሄድ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ያሉ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን እና የንግድ ምልክቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም የንግድ አጋሮቻቸውን የሚያገኙበት መድረክ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ለሺንዋ እንደተናገሩት አውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ ላኪዎችና በቻይና ቡና ገዢዎች መካከል ትስስር በመፍጠር የቡና ገበያን ይጨምራል ብለዋል፡፡
ቻይና የኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻ እንደመሆኗ በአውደ ርዕዩ ተጨማሪ የንግድ ስምምነቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃልም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡
ዳይሬክተሩ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ቡና በአይነቱና በጣዕሙ ጥራት ያለው በመሆኑ ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን ከቡናና ሻይ ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-