Fana: At a Speed of Life!

ዳግም የግፍ ቀንበርን አንቀበልም -የሲዳማ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዳግም የግፍ ቀንበርን አንቀበልም” ሲል የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።
ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ዳግም የግፍ ቀንበርን አንቀበልም
ከምንም በላይ ለነፃነቱ ቅድያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ወራሪ ጠላት በመጣበት ጊዜ ሁሉ በታላቅ አርበኝነት መንፈስ በእጅ የሚገኘውን ማኛውንም መሣሪያ በመጠቀም ጠላትን መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣት አርበድብዶ ከአገሩ ያስለቀቀበተ የትግልና የድል ታሪክ ዛሬም አገር ለማፍረስ አካባቢዎች ወሮ ሀብት ንብረታቸውን ለመዝረፍ የመጣን ጁንታና የውጭ ኃይሎች ሙከራ ከንቱ አድርጎ በመመለስ ነፃነታችንን መጠበቅ በእጃችን ያለ ዕድል መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ስለሆነም መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተነስተን በመዝመት አደጋውን መመከትና አገራችንን ማዳን ይኖርብናል፡፡
ጁንታው ወያኔ በሥልጣን ላይ በቆየባቸው 27 ዓመታት የሀገራችንን መርከብ ሳይቀር የሰረቀ የፋብሪካዎችን ማሽን ፈትቶ የወሰደ፤ ድሀ እናቶች ከመቀናታቸው ፈትተው ያዋጡትን የሁላችንም ገንዘብ ግድቡን አጠናቆ መብራት በመስጠት ከችግር ያወጣናል ብለን ስንጠብቅ በግፍ ዘርፎና በውጭ ሀገራት አከማችቶ እንደልቡ ከመዝናናቱ በላይ መልሶ ዛሬ ሀገሩን ለማፍረስና በግድ በስልጣን ላይ በመውጣት በለመደው መንገድ ለመዝረፍ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡
ጁንታው በመራባቸው በእነዚያ የግፍ ዓመታት ለዘረፋ እንዲያመቸው ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ አንዳቸው በሌላዉ ላይ በጠላትነት እንዲነሱ፤ መተባበርና አንድነት አንድጠፋ አድርጎ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ስሜት አንድዳከም ከማድረጉ በላይ የመብት ጥያቄ በሚያነሱት ላይ ያደርስ የነበረው አፈናና ግድያ ለማስታወስ የሚዘገንን ሲሆን የሲዳማን ህዝብ በግፍ ብትሩ በተደጋጋሚ ቀጥቅጦታል፡፡
ህጋዊና ህገ-መንግሥታዊ የመደራጀት ጥያቄ በማንሳቱ ብቻ ንፁሃን ሲዳማዎች ተገድለዋል፤ ተደብድበዋል፤ እንዲሁም ታስረው ተሰቃይተዋል፡፡
ጁንታው የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት መሆኑ ግልጽ ስለሆነ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተነስተውና ታግለው በላያቸው የተጣበቀውን መዥገር አስወግደው በነፃነት እና በእኩልነት የሰላም አየር መተንፈስ ከጀመሩ ጥቂት አመታት የተቆጠሩ ሲሆን የዕድገት ብልጭታዎችም መፈንጠቅ ጀምረዋል፡፡
የታየውን እኩልነት፤ ነፃነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ተስፋ በማድረግ ህዝባችን ታግሎ ያመጣዉን ለዉጥ ብልጽግና ወደፊት እንድውስደው በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጦ ስልጣን መስጠቱ ህዝቡ ጁንታው ዳግም እንዲመራዉ እንደማይፈልግና የሚመራውን መንግስት እራሱ መርጦ የሰየመ በመሆኑ ከዚህ ውጭ በኃይል ‘እኔ አመራሀለሁ’ ብሎ የሚመጣን ኃይል አንደማይቀበለው ለማንም ግልጽ ነው፡፡
በሌላ በኩል ጁንታው እንደገና ኢትዮጵያን በኃይል በመቆጣጠር ዳግም በባርነት ሊገዛን ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ በመውረር ላይ ይገኛል፡፡
በወረረባቸው አካባቢዎችም ከዚህ በፊት አንደሚያደርገው በግፍ እየጨፈጨፈ ያገኘውን ሀብት ንብረት እየዘረፈ ወደ መቀሌ በመጫን ላይ ይገኛል፡፡
በደረሰበት ቦታ ሁሉ የሚያደርገው የጥፋት ተግባሩ ሁሉም ቦታ የሚቀር ባለመሆኑ ስልጣን ይዞ የበለጠ እንዳይጨቁነንና እንዳይዘርፈን ዳግም ለግፍ ጭቆና አንገዛም ብለን ሁላችንም መዝመትና መመከት ይኖርብናል፡፡
ከዚህ አኳያ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ የሚከተለውን ወሳኔ አስተላልፏል ፡፡
በጁንታው ሥልጣን ዘመን የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለማሰከበር ላደረገዉ ትግል ቀና ምላሽ ማግኘት ሲገባዉ ግድያ እስራትና ድብደባ በጥቅሉ ዘግናኝ ግፍ በተደጋጋሚ ደርሶበታል፡፡
በመሆኑም ግፍ ከበዛባቸዉ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ታግሎ ባገኘዉ ነፃነትና እኩልነት ጥያቄዎቹ ህጋዊ ምላሽ አግኝቶ አሁን በሀገርቷ ጉዳይ በጋራ እየወሰነ የሚገኝ ሲሆን ጁንታው ዳግም ወደ ሥልጣን ወጥቶ በለመደው መንገድ የጭቆና ቀንበሩን እንድጭንበት ስለማይፈቅድ፤-
1ኛ. የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ ወይም የግፍ ጭቆና የመገዛት አደጋ በአስማማኝ መልኩ እስክንቀለብሰዉ ድረስ የቅድሚያ ትኩረት ለህልዉናዉ ዘመቻ እንድሆን፤
2ኛ/ ከምታገሉ ህዝቦች ጎን ቆመን መታገልና ጁንታው ከገባበት አከባቢ አንዳይወጣ አድርጎ ለመቅበር ዕድሜውና የጤንነት ሁኔታው የሚፈቅድለት ሁሉ ለህልውና ዘመቻ ዝግጁ እንዲሆን፤
3ኛ/ የተለየ ልምድ ያላችሁ ሰራዊቱን በግንባር ለመደገፍ በየወረዳዉ ፀጥታ ጽ/ቤት እንድትመዘገቡ፤
4ኛ/ ለህልውና ዘመቻ የሚያሰፈልገው ሎጂስቲክስ ከፍተኛ በመሆኑ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚቻል አይሆንም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጦርነቱ ባለባቸዉ አከባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመኖራቸዉና ልንደርስላቸዉ ስለሚገባ በከፍተኛ ደረጃ ሀብት ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ስለሆነም ሀብት ያላችሁ ሁሉ ካላችሁ አንስታችሁ የመከላከያ ሰራዊታችንን መደገፍና የተፈናቀሉትን መደገፍ፤ ለዚህ የተቋቋመዉ ኮሚቴ ስራዉን በሚሰራበት ወቅት ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፤
5ኛ/ የክልሉ ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል፡ ህዝቡ ተደራጅቶ የዉስጥ ሰላሙን እንዲጠብቅ፤ በአስፈለገ ቦታ ሁሉ ተዟዙሮ የሚሰራ ተጠባባቂ የጸጥታ ኃይል በፍጥነት እንዲደራጅ እና ከጎረቤት ወንድም ህዝቦች ጋር ያለዉ መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማንኛዉም መልኩ የፀረ-ሰላም እንቅስቃሴ የሚያደርግ የዉስጥና ፀጉረ ለዉጥ ሲገኝ ህዝቡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ህጋዊ እርምጃ እንድወስድ በማለት፤የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪ ያደርጋል
ድሉ የኢትዮጲያ ህዝብ ነዉ!
ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.