Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት ለ1 ሚሊየን ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ኢንፑት አውት ፑት ኤች ኬ ሊሚትድ ከተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር ለተማሪዎች እና መምህራን ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችል የፕሮጀክት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በስምምነቱ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፕሮጀክቱ በታሰበው ደረጃ መሄዱን አድንቀው በስምምነቱ መሰረት የ መጀመሪያው 1 ሚሊየን ዲጂታል መታወቂያ በዚህ ዓመት መጨረሻ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከ ኢንፑት አውት ፑት ኤች ኬ ዋና ስራ አስኪያጅ ቻርለስ ሆፕ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር በ3 ሺህ 680 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ 5 ሚሊየን ተማሪዎች እና 750 ሺህ መምህራን የዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ከ ኢንፑት አውት ፑት ኤች ኬ ጋር ከዚህ ቀደም ስምምነት መፈፀሙ ይታወሳል፡፡

የአሁኑ ስምምነትም የመጀመሪያው ዙር በመጠናቀቁ ፕሮጀክቱ ያለበትን ደረጃ በመገምገም በታሰበለት ደረጃ እና በሚጠበቀው ጊዜ ዲጂታል መታወቂያ ለማድረስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የተማሪዎች እና መምህራን ዲጂታል መታወቂያ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.