Fana: At a Speed of Life!

ለመስክ ስራ የሚያገለግሉ 15 ተሽከርካሪዎችና 300 ሞተር ሳይክሎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ለመስክ ስራ የሚያገለግሉ 15 ተሽከርካሪዎችና 300 ሞተር ሳይክሎች ለክልሎችና ተጠሪ ተቋማት ድጋፍ ተደረገ።
 
ለተሽከርካሪዎቹ ግዥ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጓል።
 
ተሽከርካሪዎቹ ለእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት የሚያገለግሉ 15 መኪኖች እና 300 ሞተር ሳይክሎች መሆናቸው ተገልጿል።
 
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ፤ ድጋፉ በተለይም የሎጀስቲክስ አቅርቦት ችግርን በመፍታት ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
 
በአብዛኛው የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት የሚካሔደው ከከተማ ራቅ ባሉ ቦታዎች በመሆኑ ባለሙያው ተሽከርካሪዎቹን በመጠቀም ለአርሶና አርብቶ አደሩ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት።
 
ክልሎች የተሰጧቸውን ተሸከርካሪዎች ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲያውሉም አሳስበዋል፡፡
 
የእንስሳትና ዓሳ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶክተር ቶማስ ቸርነት፤ በፕሮጀክቱ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የእንስሳት ዝርያን ለማሻሻል እንደሚሰራ ተናግረዋል።
 
የተደረገው ድጋፍም የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዘርፉ የተሰማሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት፡፡
 
ፕሮጀክቱ በተለይ በገጠር አካባቢ በህብረት ስራና አነስተኛ ግብርና የስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ወጣቶች ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝም ዶክተር ቶማስ ተናግረዋል፡፡
 
አሁን ላይ 10 ሺህ 566 በግል ፍላጎት የተደራጁ እና 176 ማህበራትን እየደገፈ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል።
 
ከዚህ በፊት መሰል ስራዎችን ለማገዝ 122 መኪኖችን እና 146 ሞተር ሳይክሎችን አስመጥቶ ለክልሎች ያከፋፈለ መሆኑን አስታውሰዋል።
 
ከየክልሉ ድጋፉን የተረከቡት ተወካዮችም ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የእንስሳት ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል፡፡
 
ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ተሸከርካሪዎችን ለተፈለገው ዓላማ በአግባቡ እንዲያውሉ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.