Fana: At a Speed of Life!

 እንደ በግ የታረደዉን የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችንን አንረሳውም !- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ወገኔ’ ብሎ ባገለገለው አካል እንደ በግ የታረደዉን፤ በክፉዎች ፅዋ ግብዣ መርዝ የተጋተዉን የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችንን መቼም አንረሳውም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ለ 2 አስርት አመታት ‘ወገኔ’ ብሎ በቀበሮ ጉድጓድ ዉስጥ ህይወቱን፣ ቤተሰቡን፣ ኑሮዉን አሳልፎ በሰጠለት አካል በተኛበት የታረደዉን፤ የተካደዉን፤ ከጀርባው የተወጋውን ፤ ዕርቃኑን እንዲዋረድ የተደረገውን፤ በሬሳዉ ዙሪያ ከበሮ የተደለቀበትን ያንን ጀግና የሰሜን ዕዝ ወታደር መቼም አንረሳውም ብለዋል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ፡፡

ለኢትዮጵያ ዘላለማዊ ክብር የከፈለውን ዉድ የመስዋዕትነት ጥግ ምንጊዜም በታሪክ እንዘክረዋለን ያሉት ወይዘሮ አዳነች÷ በደምህ የጨፈሩትን፤ በክቡር ሬሳህ ዙሪያ ከበሮ የደለቁትን ከሀዲያንና የእናት ጡት ነካሽ አረመኔዎች እንቀብራቸዋለን ነው ያሉት፡፡

የከፈልከዉ ዉድ ዋጋ በኢትዮጵያ የጀግኖች ታሪክ ጉልህ የሆነዉን ስፍራ ይዞ ለዘላለም ይኖራልም ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.