Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን እዝ በሽብርተኛው ህወሃት ከጀርባው የተወጋበት አንደኛ አመት ነገ ታስቦ ይውላል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን እዝ በሽብርተኛው ህወሃት ከጀርባው የተወጋበት አንደኛ አመት ነገ ጥቅምት 24 ቀን ታስቦ ይውላል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን÷ ድርጊቱ የጭካኔ ጥግ ማሳያ የታሪካችን ጥቁር ገፅ መሆኑን አብራርተዋል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዲሁም ተመራማሪው ሱራፌል ጌታሁን ÷የሽብር ቡድኑ ድርጊት መከላከያ ለዓመታት በቀበሮ ጉድጓድ ኖሮ ለትግራይ ህዝብ መከታ የሆነበት ፣በአምበጣ መንጋ ጊዜ እና በእህል ስብሰባ ጊዜ የከፈለውን ዋጋ የረሳ አረመኔያዊ ድርጊት ነበር ነው ያሉት።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ዶክተር ፍሬው ይርጋለም ደግሞ አላማው ሀገር መበተን ከዚያ የትግራይን ሪፐብሊክ በቦታው መትከል ነበር ብለዋል፡፡

በአላማ ፅናት እና በሀገር ፍቅር መነሻ ለሀገር ዋጋ የሚከተለው መከላከያ ሀገርን የማገልገል እና ሀገርን የመውደድ ጥግ ማሳያ ነውና ሁሉም ዜጋ የመከላከያን ምሳሌነት መከተል ይገባል ተብሏል።

ሀገርን ከገባችበት ችግር ለማውጣትም መከላከያ ሰራዊቱን በሙሉ አቅም መደገፍ ይገባል ነው የተባለው፡፡

በአፈወርቅ አለሙ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.