Fana: At a Speed of Life!

ሀገረ ስብከቶቹ ከሰቆጣና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስዊዲን፣ ስካንዲኔቪያን፣ ኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከቶች ከሰቆጣና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊዲንና የስካንዲኔቪያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሰሜን አሜሪካ የኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሰቆጣና አካባቢው ተፈናቅለው በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የእብናት ወረዳ መጠለያ ማዕከል ለተጠለሉ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ አጽናንተዋል።
የስዊድንና የስካንዲኔቪያን ሀገረ ስብከት በእብናት ወረዳ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች 1 ሚሊየን 36 ሺህ ብር የሚያወጣ ዘይትና ልዩ ልዩ ምግቦች፣ 134 ሺህ ብር የሚያወጣ የሕጻናት አልሚ ምግቦችን ድጋፍ አድርጓል።
በተመሳሳይም በደሴና በኮምቦልቻ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
በሰሜን አሜሪካ የኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከት ደግሞ 580 ሺህ ብር የሚያወጣ የተለያየ የምግብ ሸቀጥ በመጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጋር በስፍራው የተገኙት መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ገብርኤል አሰፋ በካናዳ ካልጋሪ የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ከግላቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የቤተክርስቲያንኗ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎትን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.