Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ተፈትና ይሆናል እንጂ ተሸንፋና ወድቃ አታውቅም” -እናት ፓርቲ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ፍላጎቴን በኃይል እጭናለሁ ብሎ ማሰብ እብደትም እብሪትም ነው ሲል የእናት ፓርቲ አስታወቀ።
ፓርቲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ ፥“አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ተፈትና ይሆናል እንጂ ተሸንፋና ወድቃ አታውቅም” ብሏል።
በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ፍላጎትን በኃይል እጭናለሁ ብሎ ማሰብ እብደትም እብሪትም በመሆኑ ሕዝቡ በተባበረ ክንድ ይመክተዋል ነው ያለው።
ወቅቱ የአገር ሕልውናን የመታደጊያ በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙና ከዚያም በላቀ መልኩ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ፓርቲው አመልክቷል።
አገር በምትጠይቀው መስክ ሁሉ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈለግም ጥሪውን አስተላልፏል።
ኢትዮጵያን ከገባችበት ቀውስ የመታደግ ሃላፊነት ‘የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው’ ያለው መግለጫው በአገር ውስጥም ሆነ በየትኛውም ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የቀድሞ ጦር ጠበብቶችን ሙያዊ ዕገዛና አስተዋጽኦ መጠቀም እንደሚገባ አመልክቷል።
‘አገራችን ብትፈተን እንጂ አትወድቅም፤ ይህ ግን በምኞት ሳይሆን በመስዋዕትነት የሚገኝ መሆኑን ሕዝቡ ተረድቶ ክንዱን ማበርታትና ለሚቀርብለት ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቋል።
“ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅት የምንሞጋገስበትም ሆነ የምንወቃቀስበት ሳይሆን ይልቁንም አገር ለመታደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንቆምበት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነት በሚሰማው መልኩ እንዲንቀሳቀስ” ሲል ነው ጥሪውን ያስተላለፈው።
የዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት የእርዳታ ተፈጥሮው ለተጎዱ በሰብዓዊነት የሚደርስ እንጂ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት የሚውል አድሏዊ ተግባር እንዳልሆነ ሊረዱ ይገባል ብሏል።
በመሆኑም በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መድረስ እንደሚገባ አመልክቷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.