የሀገር ውስጥ ዜና

ዕንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም – ጠ /ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

November 02, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ጠላቶች ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናበሥራለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ።

እንዲያውም የመሸጋገሪያ ድልድዮች ሆነው ያገለግሉናል። ዓለማችን ላይ ቁልፍ ግኝቶች የተገኙት፣ አስደማሚ ቴክኖሎጂዎች የተሠሩትና ችግር ፈቺ መፍትሔዎች የተፈጠሩት በፈተና ጊዜ ነው።

በፈተና ጊዜ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዕንቅፋትን ወደ ዕድል ለመለወጥ በሚነሡ ብርቱዎች ትጋት እንደሆነ የብዙ ሀገራት የሥልጣኔ ታሪክ ያስተምረናል ብለዋል በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

ሁላችንም ተረባርበን ይኼንን ወቅት ለመልካም ለውጥ ከተጠቀምንበት ያለ ጥርጥር መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆንበት ጊዜ ነው።

በምድር በሰማይ ብለን፣ ኃይላችንን አስተባብረን፣ ክፍተታችንን ሞልተን፣ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን፣ በኢትዮጵያ ጠላቶች ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናበሥራለን።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!