Fana: At a Speed of Life!

በኢንጂነር አይሻ የሚመራ ልዑክ በ10ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ 10ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው።

10ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አቡዳቢ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በፎረሙ ላይ በተባበሩት መንግስታት ዩ ኤን ሀቢታት ዋና ዳይሬክተር ማይሙና ሞሀድ ሸሪፍን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ የከተሞች ልማት የስራ ሀላፊዎች፣ ከንቲባዎች እና ምሁራን እየተሳተፉ ነው።

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ ፎረም ላይ የተለያዩ መድረኮች፣ የልምድ ልውውጦችና አውደ ርዕይ እንደሚካሄድም ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.