Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ማሸነፍ ሌት ከቀን በትጋት የምንሰራበት ወቅት ነው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ወቅቱ እንደ ሃገር የገጠመንን ፈተና ለመሻገር ሁላችንም በአንድነት በፅናት የምንቆምበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለማሸነፍ ቁልፉ እጃችን ላይ ነው ያሉት ከንቲባዋ ÷ ለኢትዮጲያ ማሸነፍ ሌት ከቀን በትጋት የምንሰራበት ወቅት ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

ይህም ወጣቶች መከላከያ ሰራዊታችንን በስፋት በመቀላቀል ፤ ሴቶችና የህብረተሰቡ መሪዎች እንዲሁም መላው የከተማው ነዋሪ ከምንም ስራ ቅድሚያ ለሰላም በመስጠት ከነገ ጀምሮ በእያንዳንዱ ብሎክና መንደር ተደራጅተን እራሳችንን ከወሬና አሉባልታ አርቀን አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅ የሰፈራችን ፖሊስ እና የሰላም ዘብ መሆናችንን እንድናረጋግጥ ይሁን ብለዋል።

መንግስት የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያወጣቸውን መመርያዎችና አዋጆች አክብሮ በመንቀሳቀስ ፣ ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመቆም ፣ በሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ ማንኛውንም በእጃችን የሚገኝ የጦር መሳርያ በአቅራቢያችን ባሉት ፖሊስ ጣቢያዎች በማስመዝገብ አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅ ኢትዮጵያዊ አይበገሬነታችንን እንድናሳይ ሲሉ ጥሪያቸውን አስታላልፈዋል።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በየትኛውም ሁኔታ የተገኘ የጦር መሳርያ ይወረሳል፤ በወንጀልም ተጠያቂ ያደርጋልም ነው ያሉት ፡፡

መመርያዎች አክብረን እና አስከብረን አንድ ሆነን ከቆምን አሁን የገጠመን ችግር ያለ አንዳች ኮሽታ ባጠረ ጊዜ እንደምንሻገርና የከተማችንን አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ እንችላለንም ብለዋል፡፡

”በርቱ! ካለምንም ጥርጥር ጦርነቱን በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፤ አንድነቷም ይጠናከራል፤ ጁንታውም ይቀበራል” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.