Fana: At a Speed of Life!

ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል አፈ ጉባኤ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር ከሁሉ በላይ በመሆኗ÷ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነትና አብሮነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ተናገሩ፡፡
ከጠላቶች የሀሰት ወሬ መራቅና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆም አስፈላጊ መሆኑን ነው አፈጉባኤዋ አጽንኦት የሰጡት፡፡
ሀገር የማፍረስ ዘመቻውን ጠላት አቅሙን አሟጦ እየተጠቀመ የሚገኝ በመሆኑ÷ የምክር ቤት አባላትና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀገርን የመታደግ ዘመቻ ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱም በዛሬ ውሎው የ6ኛው ዙር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ረቂቅ ቃለ ጉባኤን መርምሮ ማፅደቅ በቀረበው ሞሽን ላይ ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን÷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄን ሂደት የሚያመላክት ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የስልጣን ርክክብ እንደሚኖር ተመላክቷል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው

ፎቶ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.