Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት የሰሜን እዝ በህወሓት የተጨፈጨፈበትን አንደኛ አመት አሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሰሜን እዝ በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከጀርባው የተወጋበትን አንደኛ አመት በዛሬው ዕለት አስበዋል።
ተቋማቱ አሸባሪው ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በፈጸመው ክህደት መስዋዕት ለሆኑ የሠራዊት አባላት ” አልረሳውም ፤ እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ” በሚል መሪ ቃል ነው አስበው የዋሉት።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “ይህን ጊዜ እናልፈዋለን ሀገርም እንደ ሀገር ይቀጥላል” ብለዋል። ጦርነቱን ቶሎ አጠናቆ ወደ ስራ መመለስ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በፈጸመው ክህደት የተሰው የሰራዊት አባላትን አስበዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች፣የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ሠራተኞች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ሠራተኞች፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣የግብርና ሚኒስቴር በሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት “አልረሳውም፤ እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ” በሚል መሪ ቃል አስበዋል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ÷ኢትዮጵያውያን በሁሉም ዘርፍ ተደራጅተው አገራቸውን ከአደጋ መጠበቅ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሻማ ማብራት እና የመታሰቢያ የፀሎት መርሀ ግብርም ተከናውኗል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.