Fana: At a Speed of Life!

”ዕድሜዬ ገፍቷል ብዬ ሀገሬ ስትፈርስ ቆሜ አላይም!”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ዕድሜዬ ገፍቷል ብዬ ሀገሬ ስትፈርስ ቆሜ አላይም!’ ሲሉ የመንግስትን የክተት ጥሪ በመቀበል ለመዝመት የተዘጋጁ የጂንካ ከተማ ነዋሪ ተናገሩ።

የከተማው ነዋሪ አቶ አባ ሺችሚ ÷ “ጠላት ሀገር ለማፍረስ ሲዘምት እኔ እንዴት ቤት እቀመጣለሁ?” ሱሉ በቁጭት ተናግረዋል ።

ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮውን ለማሳካት ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ መሆኑ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
አዛውንቶችና ሴቶች ጭምር የጥፋት ተልዕኮው አካል ሆነው መገኘታቸው ተገቢ አለመሆኑን አመልክተዋል።

”በ60 ዓመቴ ሀገር ለማዳን የማልዘምትበት ምክንያት የለም” ያሉት አቶ አባ ÷”ዕድሜዬ ገፍቷል ብዬ ሀገሬ ስትፈርስ ቆሜ አላይም” ብለዋል።

”በህልውና ዘመቻው ለመሳተፍ ዝግጁ ነኝ” ሲሉ የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.