Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ነገ በሚኒስትሮች ም/ቤት የተዘጋጅው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይቀርብለታል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ነገ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቁም የማይቻል ሲሆን፣ ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡
 
በዚሁ አንቀጽ 2(ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክረር ቤት መቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል፡፡
 
በመሆኑም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.