ደቡብ ሱዳን በአቪየሽን ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷን እንደምታጠናክር ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የትንስፖርት ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለሱዳን መረጋጋት እና በደቡብ ሱዳን የአቪየሽን ኢንዱስትሪን ለማጠናከር የተጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት ሚኒስትርም ÷ ኢትዮጵያ ችግሮቿን በራሷ መፍታት የምትችል መሆኑንና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በአቪየሺን ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!