የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ ያሰለጠናቸውን የሚሊሻ አባላት አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ በወታደራዊ ብቃት ሲያሰለጥናቸው የቆዩ የሚሊሻ አባላትን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በጌዴኦ ዞን የተጠናከረ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር እንዲቻል የሚሊሻ ኃይሉን አቅምና ብቃት መገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገልጿል፡፡
የዞኑ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አየለ በህብረተሰቡ ውስጥ ህገ-ወጥ ተግባር በመፈጸም ህዝብን የሚያሸብሩ ፀረ-ሰላም ሀይሎችን ለመመከት የሚሊሻውን ሃይል በእውቀትና በአካል ብቃት መገንባት ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
፡ የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሃላፊ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በበኩላቸው÷ የሚሊሻ ኃይሉ ሕብረተሰቡን አስተባብሮ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከልና ተግባሩን በብቃት ለመወጣት ያሳያችሁት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ማለታቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የካማሺ ዞን ስልጠና ያጠናቀቁ የሚሊሻ አባላትን አስመርቋል፡፡
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ለጸጥታ ስራው እገዛ የሚያደርጉት የሚሊሻ አባላት የክልል እና የዞን አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መመረቃቸውን የቤኒሻንጉል ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!