Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንዱስትሪው 42 ነጥብ 75 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከዘይት አምራች ኢንዱስትሪው 42 ነጥብ 75 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ፡፡
በሩብ ዓመቱ 42 ነጥብ 85 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 42 ነጥብ 75 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን÷ የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በማምረት ላይ ለሚገኙ ፋብሪካዎች በተደረገው ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ የእቅዱን 99 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ተገልጿል፡፡
የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በማምረት ላይ ላሉ 14 ፋብሪካዎች እንዲሁም በግንባታ ላይ ላሉ 3 ፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ የግብዓት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ ለዘይት አምራች ፋብሪካዎች 35 ሺህ 742 ቶን ድፍድፍ ዘይት መቅረቡን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ጥናት ድጋፍና ክትትል ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሎቤ ገልጸዋል፡፡
የዘርፉን ሥራዎች ለማሳካት የሚያግዙ የጥናት ስራዎችን በማከናወን በአምራቾች የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ የአመራሩንና የፈፃሚዎችን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ከፍተትን ለማጎልበት ስልጠና መሰጠቱንና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ማስረዳታቸውን ከወድሞው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.