Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን መፈናቀል ከመሠረቱ ለመግታት መዝመት ይገባል – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል ከመሠረቱ ለማስቆም በመንግስት የቀረበውን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር መዝመት እንደሚገባ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በክልሉ በፈጸመው ወረራ የሚፈናቀሉ እና ለምግብ ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት ተዳርገው ሕይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን አስታውቋል።
ለሰብአዊነት እንቆማለን የሚሉ ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶችም ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ችግሩ መባባሱን አስታውቋል።
ወደ ክልሉ ገብተውም የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እንዲሰሩ ጠይቀዋል። ችግሩን በዘላቂነት እንዲፈታ የጥፋት ቡድኑ በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ጠራርጎ በማስወጣት ዜጎች ማኅበራዊ እረፍት የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከፌደራል መንግስት፣ ከተወሰኑ ረጂ ድርጅቶችና ከኅብረተሰቡ የሚያገኘውን የምግብ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃዮች በፍትሃዊነት ለማዳረስ እየሰራ መሆኑ በመድረኩ አመላክቷል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.