በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ቱርክ የኢትዮጵያ የልማት አጋር ናት – ዶክተር ፍጹም አሰፋ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና በቱርክ ልማት ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊዎች መካከል ውይይት ተካሂዷል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በዚህ ወቅት ለቱርክ የልማት እና ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በልማት እቅዷ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች አስረድተዋል።
በተለይ በአቅም ግንባታ፣ በትምህርት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያላትን አስተዋጽኦ እንዲሁም አገራቱ ያላቸውን ቁርኝት አውስተዋል።
የሁለቱ አገራት አጋርነት አሁን ካለው ጎልብቶ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በማንሳት በሁለቱ አገራት በኩል መደረግ ስለሚኖርባቸው ጉዳዮችና አቅጣጫዎች ላይ ምክክር መደረጉን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!