Fana: At a Speed of Life!

ከሃዲውን የህወሓት ቡድን ለመፋለም መዘጋጀታቸውን የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሃዲውንና ወራሪውን የህወሓት ቡድን እስከ ግንባር ድረስ ዘምተው ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ።
 
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግፍ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ”አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ!” በሚል መሪ ቃል በሐረር ከተማ ተካሂዷል።
 
በመርሃ ግብሩ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ደም ለግሰዋል፡፡
 
ከሃዲው የህወሓት ቡድን አምና በሠራዊቱ ላይ የፈጸመው ግፍ የፈጠረባቸው ቁጭት የሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት በመዝመት ጭምር ለማስከበር የበለጠ እንዳነሳሳቸው የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
 
የጥፋት ሃይሉ ሰሜን ዕዝ አባላት ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ ሳይበቃው አሁንም ወጣቶችን በመጨፍጨፍ፣ ሴቶችን በመድፈር ፣ ቅርሶችን በማውደም እና የሃይማኖት ተቋማትን በማቃጠል አሸባሪነቱን እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
በክልሉ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ በተከናወነው መርሃ ግብር ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
 
ካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.