Fana: At a Speed of Life!

ጀግኖችን ስናስብ የሽብር ቡድኑን ግብዓተ መሬት ለመፈጸም ቃል በመግባት ነው-የደባርቅ ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 24ን ስናስብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሽብር ቡድኑን ግብአተ መሬት በተባበረ ክንድ ለማጠናቀቅ ቃል በመግባት ነው ሲሉ በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

”አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ  ነዋሪዎቹ ዕለቱን በህሊና ጸሎት አስበውታል፡፡

ነዋሪዎቹ  ÷ የህወሓት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ክህደት ሀገረ አፍራሽነቱን ያጋለጠ እና ታሪክ ይቅር የማይለው እኩይ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ዕለቱን የሚያስቡት የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ክህደት የፈጸመበት ቀን መሆኑንና  ሀገር የማፍረስ ዓላማው እንዳልተሳካ በማሰብ ብሎም አሸባሪ ቡድኑ በዓለም አደባባይ እንዲጋለጥ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ÷”ጥቅምት 24ትን ስናስብ ፣ የሽብር ቡድኑን ግብአተ መሬት በተባበረ ክንድ ለማጠናቀቅ ቃል በመግባት እና ህዝባዊ አንድነታችን በማጠናከርም ነው ብለዋል።

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሀኑ ፀጋዬ በበኩላቸው ÷ ህወሓት በሀገርና በህዝብ ላይ የፈጸመው ክህደት ኢትዮጵያዊያንን ከማስቆጣት ባለፈ አንድ ሆነው ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል ቁጭት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ÷ይህን የውጭ ሀይል ተላላኪ ባንዳ ነቅለን ለመጣል በእልህ፣ በወኔና በህብረት ከተንቀሳቀስን ድላችንን የምናበስርበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.