የሀገር ውስጥ ዜና

የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 25 ተራዘመ – የአዲስ አበባ ፖሊስ

By Tibebu Kebede

November 03, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም መራዘሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአስራ አንዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ዛሬና ትላንት አስመዝግበዋል፡፡

የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ ምክንያት ምዝገባው እስከ ነገ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም የተዘራዘመ ስለሆነ በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ እሳስቧል።

የጦር መሳሪያ በማያስመዘገቡ ግለሰቦች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን እንዲሁም የጦር መሣሪያው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!