በመዲናዋ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ አመራሮች ሽኝት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሃገር መከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ አመራሮች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሽኝት እያደረገ ነው።
“ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” በሚል መሪ ቃል ነው ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጡ በርካታ አመራሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ሽኝት እየተደረገላቸው የሚገኘው።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የወጣቶች የድጋፍ መርሐግብር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ አለሙ፣ ከፍተኛ አመራሮች እና በርካታ ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡
ህዝባዊ ዘመቻውን ለመምራት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ አመራሮች እና የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ በርካታ ወጣቶች ሽኝት እየተደረገላቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቆንጂት ዘውዴ