Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባው ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሔደው 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በሀገር ህልውና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ያወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/14 ለማጽደቅ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ለማጽደቅ እየተወያየ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.