Fana: At a Speed of Life!

ከ40 በላይ ሃገራት የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማቆም ቃል ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ40 በላይ ሃገራት የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማቆም መስማማታቸው ተገለፀ።

ፖላንድ፣ ቬትናም እና ቺሊን ጨምሮ ዋና የድንጋይ ከሰል አምራች የሚባሉ ከ40 በላይ ሃገራት በግላስኮ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ምርቱን ለማቆም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በአንጻሩ አውስትራሊያ፣ህንድ፣ቻይና እና አሜሪካ የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማቆም የቀረበውን ስምምነት አልፈረሙም።

የሃገራቱ ውሳኔ ዓለምን ከብክለት ለመታደግ እና ከአካባቢ ጥበቃ አንጻር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የድንጋይ ከሰል ምርት ለአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.