አየር ኃይሉ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ እየመታ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከመቼው ጊዜ በላይ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታትና ስርዓተ ቀብሩን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ በብቃት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገራ ሌሊሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥ አየር ኃይሉ ከመቼው ጊዜ በላይ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታትና ስርዓተ ቀብሩን ለመፈፀም የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው።
ተቋሙን በቴክኖሎጂም ሆነ በሰው ኃይል አደረጃጀት አቅሙን ለማሳደግ ከሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ጎን ለጎን በሀገር ላይ የተቃጣውን ወረራ ለማክሸፍም አኩሪ ተግባርና ታላቅ ጀብዱ እየፈፀመ መሆኑን አስረድተዋል።
አየር ኃይሉ የአሸባሪው ሕወሓት ቡድንን ሞት እንዲፋጠን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ገልጸው፤ የአሸባሪ ኃይሉን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ድባቅ እየመታው እንደሚገኘም ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People reached
0
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
Like
Comment
Share