Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በሩብ አመቱ ከ36 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት ለ36 ሺህ 764 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በመጀመሪያው ሩብ አመት ወደ ስራ ከገቡ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለ14 ሺህ 396 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ነው ለ36 ሺህ 764 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የተቻለው፡፡

በዚህም ለ2 ሺህ 587 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን÷ ለ34 ሺህ 177 ዜጎች ደግሞ ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ 690 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ በተሰራ ስራ 1 ሺህ 416 የህብረተሰብ ክፍሎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል በበጀት አመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት 29 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በክልሉ ካቢኔ ጸድቆ ለባለሃብቶች እንዲተላለፍ መደረጉን ከደቡብ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.