የባንዳዎች የመጨረሻው ታሪክ መቃብር ይሆናል -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ታሪክ መሸነፍ አይፈቀድም ሲሉ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ፥ የባንዳዎች የመጨረሻው ታሪክ መቃብር ይሆናልም ነው ያሉት።
በዛሬው ዕለት “ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነት እከፍላለሁ ” በሚል ህዝባዊ ዘመቻውን ለመምራት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ አመራሮች እና የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ በርካታ ወጣቶች ሽኝት መርሐግብር መካሄዱን አስታውቀዋል።
ይህ አኩሪ ትውልድ ሀገሩን ከሽፍታው ቡድን ለመታደግ ያሳየው ወኔ እና ቆራጥነት የሚደነቅ ነዉ ሲሉም ገልጸዋል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!