Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊው የኖክ ኩባንያ ባለቤት በጅቡቲ የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ የሆነው ኖክ በሃገረ ጅቡቲ የ1ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ለመጀመር ስምምነት ላይ ፈፅሟል፡፡

በጎረቤት ሀገራት ኢንቨስትመንቶችን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለውን ጥረት ተከትሎ የኢትዮጵያዊው ባለሃብት ንብረት የሆነው ኖክ ጅቡቲ ከቻይና ኮንስትራክሽን ጋር የአገልግሎት መስጫ ጣቢያውን በከፍተኛ ደረጃ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

የጅቡቲ ኢነርጂና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ፣ የጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኢድ ኑህ ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሀኑ ፀጋዬ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኖክ ጅቡቲ ስራ አስኪያጅ ፋሲል ወልደማርያም በዚህ ወቅት ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለማመቻቸት ላደረጉት ድጋፍ የኢነርጂ ሚኒስትሩን እና የኢትዮጵያ አምባሳደር አመስግነዋል፡፡

አክለውም ኖክ ጅቡቲ ከመንግስት እና ከግል አጋሮች ጎን ለጎን ለጅቡቲ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀውላቸዋል።

ፒኬ 12 በመባል በሚታወቁ አካባቢዎች ኖክ ጅቡቲ በ2021 መጀመሪያ ላይ በተጀመረው አዲስ የአገልግሎት ጣቢያ ግንባታ ላይ ኢንቨስት ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.