Fana: At a Speed of Life!

የጥቅምት 24 ሰማዕታት በደቡብ ሱዳን ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአሸባሪው ህወሐት ለተሰዉ የጀግናው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሰማዕታት ቀን በደቡብ ሱዳን ጁባ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ታስቦ ዋለ፡፡
ዝክረ ሰማዕታቱ የታሰበው “ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሰዉ ጀግኖቻችን” በሚል መሪ ሀሳብ መሆኑ ተመላክቷል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት አምባሳደር ነቢል ማህዲ፥ ከ20 ዓመታት በላይ ከቤቱና ከቤተሰቡ ተነጥሎ ጠላት ሲመጣ የሚመክት፣ አዝመራ ሲደርስ የሚያጭድ፣ ት/ቤትና የጤና ተቋማትን በራሱ ገቢ ይገነባ የነበረን ሠራዊት ሰዋዊ ባልሆነ መልኩ በአሸባሪው ህወሓት የተሰጠው ምላሽ በታሪክ የማይዘነጋ መሆኑን ገልጸው፥ የተከፈለው መስዋዕትነት ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስከበር ነው ብለዋል።
ጁንታው በተላላኪነት የወሰደው ሀገር የማፍረስ አጀንዳን ለመቀልበስ በዚህ ወሳኝ ወቅት አንድነታችንን በመጠበቅ፣ የገባነውን ቃል በማደስ ፣ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የኤምባሲው ሠራተኞች፣ የሚሊቴሪ አታሼና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ጁባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
75
Engagements
Boost Post
67
4 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.