የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የልዩ ሀይል ኮማንዶዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ለ36ኛ ዙር የልዩ ሀይል ኮማንዶዎችን አስመረቀ።
የልዩ ሀይል ዘመቻዎች ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሹማ አብደታ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ፥ህዝቦችን በማጣላት ሀገሪቷን በተለያየ መልኩ ሲዘርፍና ሲያዋርድ የነበረውን ሽብርተኛ የህወሖት ቡድን ለማጥፋት ተመራቂ የልዩ ሀይል ኮማንዶዎች ሀላፊነት አለባችሁ ብለዋል።
ኢትየጵያን የከበቧትን የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ለማስወግድ በፍጹም ጀግንነት እየተሰራ እንደሆነ ዋና አዛዡ ገልጸዋል።
ተመራቂ ልዩ ሀይል ኮማንዶዎች ያላቸውን የግዳጅ ዝግጁነትና የውጊያ ስልቶችን ትርኢት ከፍተኛ የጦር መኮንኖቹ ምልከታ አድርገዋል።
የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ልዩ ሀይል ኮማንዶዎችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን አገሪቷን ለመታደግ መሰረታዊ የኮማንዶ ተመራቂዎቹ ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!