ለቦንጋ ገብረፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ የቦታ ርክክብ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ለጤና ባለሙያዎች መኖሪያና ለሌሎች መሰረታዊ የህክምና አገልግሎቶች የሚውሉ የህንፃዎች ማስፋፊያ ቦታ ርክክብ ተደርጓል።
የግንባታ ስራው ከ158 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት ሲሆን÷ ሙሉ ወጪው በክልልና በፌደራል መንግስት እንደሚሸፈን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ፍቅረማርያም ጳውሎስ ገልፀዋል።
ህንፃዎቹ በአጠቃላይ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ ሲሆን÷ በፊት የነበረውን የመኖሪያና የህክምና አገልግሎት መስጫ ቦታ ችግር ይቀርፉል ነው የተባለው፡፡
ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከተቋራጮች ጋር የውል ስምምነት መፈረሙን ደሬቴድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!