Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ለሚገኙ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በተለያዩ የአመራር እርከን ላይ ለሚገኙ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ ተደርጓል፡፡

ገለፃውን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ አድርገዋል።

በገለፃው የሀገር ህልውናን ለማስከበር እና ሀገርን ለማዳን የክልሉ አመራሮች ከህዝቡ ጋር እንዲሰሩ ተመላክቷል።

በተለይ የህዝቡን ሰላም ለማወክ በተለያዩ ስውር ሀይሎች የሚደረጉ ሙከራዎችን አመራሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን በጋራ ሊከላከል እንደሚገባም ተመክሮበታል።

አቶ ሙስጠፌ÷ በአሁኑ ወቅት ህዝቡ ሰላሙን እንዲያጠናክር ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ÷ የዕለትተእለት ስራውን በማከናወንም ይህንን ጊዜ በጋራ ማለፍ እንደሚገባ መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.