የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ ÷ ሀገራችን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በሰሜኑ ክፍል የተከፈተባትን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ኮሚሽነሩ ÷ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋጥ እና በሀገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማስተግበር በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የክልሉ መኅበረሰብም አስፈላጊ ካልሆኑ መረጃዎች እራሱን በመጠበቅ የክልሉን እና የአከባቢውን ሠላም በንቃት እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሽብርተኛው የህወሓት ብድን በሀገር እና በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን በደል እና ጫና እስከወዳኛው ለማስቆም የሁሉም ቀና ትብብርም ያስፈልጋል ብለዋል – ኮሚሽነሩ።
የክልል ልዩ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር መሀመድ ÷ ኅብረተሰቡ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን የገለጸው የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ነው፡፡