የሀገር ውስጥ ዜና

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው

By Feven Bishaw

November 04, 2021

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡

ማብራሪያውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና በፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እየሰጡ ነው። አምባሳደር ሬድዋን÷ ማብራሪያው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ብዥታውን ለማጥራት ይረዳል ብለዋል።