ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸጉረ ልውጦችን በመለየት ለአካባቢያችን ሰላም በትኩረት በመሥራት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ሲሉ የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ÷ አሁን ላይ በሀገሪቱ ከተጋረጠው አደጋ ለመሻገር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢዘገይም መታወጁ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለተፈጻሚነቱ ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ዴቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡
ሀገሪቱ በጥፋት ኃይሎች አትፈርስም፤ አዋጁ የፀጥታ ቁጥጥሩን ለማጠናከርና ሀገሪቱንም ለማፍረስ ከሚቃጣው ሀይል ለመጠበቅ እንደሚረዳም ነው የገለጹት፡፡
ሕዝቡን ሲጨቁን የኖረው ህወሓት ዳግም ወደ ስልጣኑ እንዳይመለስ በአስፈላጊው ሁሉ ለመደገፍና ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን÷ ለዚህም ዕድሜው የሚፈቅደው ሁሉ እስከ ግንባር በመዝመት ሀገሪቱን መታደግ አለበት ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!