Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህወሓት እየፈፀመ ያለውን ሽብር ሊያወግዝ ይገባል – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ላጋጠማት ችግር ዋና ተጠያቂው ህወሓት መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን አብራርተዋል።

በተዛቡ መረጃዎች ላይ ተመስርተው በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያልተገባ ጫና እየፈጠሩ ያሉ አካላት እውነታውን በመረዳት አካሔዳቸውን ቆም ብለው መፈተሽ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የሀሰት መረጃ ከመስማት ታዕቅቦ መሬት ላይ ያለውን እውነታ መመርመር እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኗንም አብራርተዋል ።

በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ በበኩላቸው ÷ዴንማርክ ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ጊዜ የዘለቀ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላት ጠቁመው÷ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ እያደረገች መሆኗንም ጠቅሰዋል ።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ በተፈጠረው ቀውስ በርካታ ለችግር የተጋለጡ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳዩ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.