Fana: At a Speed of Life!

ከህወሓት እና ሸኔ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ እንደገለጹት÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ አስቀድሞ የክልሉ ፖሊስ የተጠናከረ የክትትል ስራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

ግለሰቦቹ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበራቸው ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሰረት ከጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት በሀሰት ወሬ ሀገርን ለማሸበር ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ÷ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈጸመውን ጥቃት ለመድገም በድብቅ ሲዘጋጁ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ግለሰቦቹ ላፕቶፕ፣ ኮምፒዩተር እና ሌሎችንም ቁሳቁስ ይዘው በነዋሪው ላይ ሽብር ለመፍጠር የሚያስችል የፈጠራ ወሬዎችን የያዙ ተንቀሳቃሽ ምስል ሲያዘጋጁ ተደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

ኅብረተሰቡ ስንቅ ከማዘጋጀት ጀምሮ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን መቆሙን አስታውቀዋል፡፡

ህብረተሰቡ በተለይ ለአሸባሪው ህወሓት የፈጠራ ወሬ ሳይደናገጥ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልና በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲንግ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር እየሰሩ መሆናቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነር አብዱልአዚም÷ ለሥራቸው አጋዥ የሆኑ የሎጅስቲክ አገልግሎቶችን በጋራ እየተጠቀሙ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በመተከል ዞን በኩል ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ባለው ቅንጅት ዞኑ ወደ መረጋጋት እንዲመጣ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይሄው ትብብር ተጠናክሮ ቀጥሏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.