የሀገር ውስጥ ዜና

ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችንና ‘ማህበራዊ አንቂ ነን’ የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታወቀ

By Meseret Awoke

November 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና ‘ማህበራዊ አንቂ ነን’ የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታውቋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት ያቀረበውን ሀገርን የመታደግ ጥሪ ተከትሎ ህዝቡ እና የመንግስት ሰራተኛው በነቂስ ዘመቻውን እየተቀላቀለ መሆኑን ገልጿል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ÷ የህብረተሰብን ሰላም እና ደህንነት የሚያውኩ ሆነው እስከተገኙ ድረስ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ አይታገስም ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!