ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪውን ተከትሎ እየተመመ ያለው ህዝብ ያሳየው ምላሽ በእጅጉ የሚደነቅ ነው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪውን ተቀብሎ እየተመመ ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ተጋድሎ የጥፋት ኃይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ያላትን ዝግጁነትና ተግባር የሚያመለክት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሁን ባወጣው መግለጫ፥ በቅርቡ በፌደራልና የክልል መንግስት አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ ለመላው ኢትዮጵያውያን ለቀረበው ጥሪ መላው ህዝባችን በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ያሳየው ምላሽና ተነሳሽነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብሏል፡፡
በጊዜያዊ ድሎች መወራጨት በጀመሩት የጥፋት ኃይሎች ላይ የማይናወጥ ዘላለማዊ ድል በማስመዝገብ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ያለብን አሁን ነውና ሁላችንም በአንድነት እንቁም ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።
በቁጣ የተነሳሳው የህዝብ ማዕበል ያስበረገገው የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የመጨረሻ ያሉትን የሽብር ወሬ በማሰራጨት መጠመዳቸውን የጠቆመው የመንግስት መግለጫ፥ ቁልፍ ኢላማቸው አድርገው የወሰዱት በአመራሩ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር፣ ፍርሃት እንዲነግስ የማሸበር ስራ ውስጥ መግባታቸውን ነው ያመለከተው፡፡
ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ እንደሚገኙ ጠቅሶ፥ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ የውጭ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ ያስጠንቅቋል፡፡
የኢትዮጵያውያንና የወዳጅ ሀገር ሚዲያዎች ለህብረተሰባችን ትክክለኛውን መረጃ በወቅትና በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡ መንግስት በመግለጫው ጠይቋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!