Fana: At a Speed of Life!

ምርኮኛው የሽብር ቡድኑ የክ/ጦር አዛዥ በደሴ ግንባር ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብናል አለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክ/ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝም ነው ምርኮኛው ጉዕሽ ገብረ የተናገረው።

የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ተናግሯል ።
አሸባሪው ትህነግ ሀገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ተቆጥሯል።

ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል።

የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል።

በዚህ ግንባር ሰራዊታችን ባደረገው ዘመቻም በርካታ የጠላት ሃይልን የደመሰሰ ሲሆን በርካቶችንም ማርኳል። ከተማረኩት ውስጥም የ ሜይዴይ ክ/ጦር አዛዥ የሆነው የ64 አመቱ ኮ/ል ጉዕሽ ገብሩ ይገኝበታል።

እንደ ምርኮኛው ገለፃ ÷ የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ሃይል ዲስፒሊን የሌለው በመሆኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል።

የሽብር ቡድኑ ያሰባሰበው የሰው ሃይል ብዛት ከታጠቀው የመሳሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ አብዛኛውን የሰው ሃይሉን በባዶ ዕጅ በማሰለፍ የጥይት ሲሳይ እያደረገው እንደሚገኝም ተናግሯል።

የትህነግ አመራሮች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ፣ በትግራይ እድሜውንና ህይወቱን በሰጠው የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የፈፀሙት የክህደት ተግባር ለአሁናዊ ምስቅልቅል እንደዳረጋቸው የገለፀው ምርኮኛው በድርጊቱም እንዳዘነ ጠቁሟል።

በአሁኑ ሰዓት በሽብር ቡድኑ አመራሮች እብደትና ቅሌት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ የሰላም እጦትና ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለፀው ምርኮኛው ፣ የብሽር ቡድኑ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል ብቸኛው መፍትሄ እንደሆነ መናገሩን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.