Fana: At a Speed of Life!

የተቃጣብንን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በጋራ እንመክት – የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ም/ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)እጅግ የተቀናጀ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም ፡-

እጅግ የተቀናጀ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ ተጀምሯል።

በኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት እየጦፈ የሚሄድበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን።

ዜጎችም በመንግስት ኃላፊነት ላይ ያሉም በደንብ ልብ ልንል የሚገባን ሁኔታ ከፊታችን እየመጣ ነው።

አሸባሪው ቡድን እና ጋላቢዎቹ በየሚዲያዎቻቸውና የዲጂታል ሰራዊት ቅጥረኞቻቸው የተቀናጀ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሊያጧጡፉ ተዘጋጅተዋል።

ይህ የመረጃ ውጊያ ልዩ ልዩ ዘዴ የሚከተል ቢሆንም አምስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረ ነው፦

1ኛ- ዜጎች በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጡና ከመንግስት ጋር መተባበር እንዲለግሙ /እንዲያቆሙ ታሳቢ ያደረገ፤

2ኛ- የአሸባሪው ኃይሎች አዲስ አበባን ለመቆጣጠር “ይሄን ያህል ቀራቸው” በሚል በዜጎች ላይ መረበሽ እንዲፈጠርና መንግስት ውጣሬ ውስጥ እንዲወድቅ ያለመ፤

3ኛ- የመንግስት ኃላፊዎች ሀገር ጥለው እንዲሸሹ ከፍተኛ ቅስቀሳ ይኖራል (ጥገኝነት ለመስጠትም ግፊት ይኖራል – ከተሳካላቸው ይጠቀሙባቸዋል)

4ኛ- መከላከያ ውጊያ እንዲያቆምና ትጥቁን እንዲፈታ ከፍተኛ ጥሪ ይካሄዳል

5ኛ- በጥቅሉ ሁሉ ነገር እንዳለቀለትና እንዳበቃለት እጅግ የተቀናጀ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለማካሄድ ጅምር አለ።

ይህ ሁሉ የሚሆነው ህወሓት ደጀን ከሚለው አካባቢ ርቆ በወገን ሰራዊት ቅንፍ ውስጥ የሞት ሽረት ትግል በሚያካሂድበት ወቅት ሲሆን ÷ የፕሮፖጋንዳው ዋና አላማ በጦርነቱ ያበቃለት የሽብር ቡድን የመጨረሻ እድሉን እንዲሞክር መሃል ሀገርን በማሸበር የወገን ኃይል በወሬ የሚፈታበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት ነው።

ከዚች ሰዓት ጀምሮ ይህን እውነታ እውቀን ሁላችንም በቻልነው አቅም መግጠም አለብን! ትዊተር የሌላችሁ ክፈቱ – ከፍታችሁ የተዋችሁት በሚገባ ተጠቀሙበት።

በፈስቡክም ዜጎች በሽብር ቡድኑና በጋላቢዎቹ ወሬ እንዳይረበሽ በንቃት የስነልቦና መረጋጋት በሚፈጥሩ መረጃዎች አየሩን መያዝ ያስፈልጋል።

‘ኦፍላይን’ ያሉ ዜጎችም በሚነዛው ወሬ እንዳይረበሹ በተቻለን አቅም ሁሉ የመረጃውን ውጊያ መጋፈጥ ግድ አለብን! ስለሰሜን ዕዝ ተቆጭተን እኔም ወታደር ነኝ ካልን ዘንዳ ቢያንስ እጃችን ላይ ያለውን መሳሪያ (ስልካችንን) ተጠቅመን የመረጃውን ውጊያ በተባበረ ክንድ እንመክት!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.