Fana: At a Speed of Life!

ለሸኔ ሲላላኩና በግብረ አበርነት ይሰራሉ ተብለው የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልልን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተጠናከረ የጸጥታ ማስከበር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ፖለስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በጋምቤላ ክልል የአሸባሪቹ ህወሓት እና ሸኔ ተላላኪዎች የጥፋት ድርጊት እንዳይፈጽሙ በመቆጣጠር ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የተጠናከረ የጸጥታ ማስከበር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

ኮሚሽኑ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ባደረገው ክትትል ለሸኔ በተላላኪነትና በግብረ አበርነት የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ እንዳሉት ÷ እራሱን “ጋነግ” በማለት የሚጠራው የሽብር ቡድኖቹ ተላላኪ በክልሉ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር ተዳጋጋሚ ሙከራዎች እያደረገ ነው።

የሽብር ቡድኖቹ ሀገር ለማፍረስ የጀመሩትን እኩይ ሴራ በጋምቤላ ክልል በተላላኪዎች አማካኝነት የጸጥታ ችግር ሊያስፈጽሙ ስለሚችሉ ኮሚሽኑ ከሌሎች የጽጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የጥበቃና የክትትል ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በተደረገው ክትትልም በጋምቤላ ከተማ የሸኔ አባል እንደሆኑ የተጠረጠሩ አስር ግለሰቦችና ለሽብር ቡድኑ ስንቅ ለማቀበል ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሰባት ግብር አበሮችን ትናንት ምሽት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሰታውቀዋል።

ኮሚሽነር አቡላ ክልሉ ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተይዞ የሽብር ቡድኖቹ ተላላኪ የሆኑ ሰርጎ ገቦች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የጸጥታ አካላት ስምሪት መደረጉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.