Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ለህልውና ዘመቻው 100 ሚሊየን ብር የሚገመት የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጎንደር ከተማ በአይነት 50ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ፤ 50ሚሊየን ብር ለህልውና ዘመቻው ስንቅ ለማዘጋጀት ታቅዶ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ እንደተናገሩት ÷ ባለፉት ጊዜያት የከተማው ነዋሪ ለህልውና ዘመቻው ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወራሪውን የህወሓት ሀይል ለመመከትና ለመደምሰስ በግንባር የሚዘምቱ የከተማዋ ነዋሪዎች በርካታ መሆናቸውን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው ÷ የክልሉ መንግስት ያወጣውን የክተት ጥሪ ህዝቡ የተቀበለበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ተቀዛቅዞ የነበረው ለወገን ጦር የሚደረገው ድጋፍ መነቃቃት የታየበት መሆኑን ያመለከቱት አቶ ባዩ ÷ በስድስት ክፍለከተሞች በተለያዩ አደረጃጀቶች ስንቅ የማዘጋጀትና በገንዘብ ድጋፍ የማድረጉ ተግባር በተጠናከረ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

በከተማ ደረጃ በአይነት 50ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ 50ሚሊየን ብር ለህልውና ዘመቻው አገልግሎት የሚውል ስንቅ ለማዘጋጀት ያቀደው ከተማ አሰተዳደሩ ÷ ይህም በከተማው ማህበረሰብ ዘንድ በጎ ምላሽ ማግኘቱን ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።

ተግባሩ በሁሉም ክፍለከተሞች የተጀመረ መሆኑን አስረድተው ÷ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምልከታ ባደረገባቸው ጃንተከል፣ ዞብል እና አራዳ ክልለከተሞች በሴቶች አደረጃጀት ስንቅ የማዘጋጀቱ ተግባር በጥሩ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ተመልክቷል።

በከተማ ደረጃ አሁን የታቀደውን 100ሚሊየን ብር ስንቅ የማዘጋጀት ዕቅድ ለማሳካትና አሸባሪውን ህወሓት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የከተማው ማህበረሰብ ሀገራዊ ሀላፊነቱን መወጣቱ እንዲቀጥል ምክትል ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።

በኤልያስ አንሙት

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.