የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ከተማን ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ ጠንካራ አደረጃጀት ተፈጥሯል – ፖሊስ

By Tibebu Kebede

November 04, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማን ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ ጠንካራ አደረጃጀት ተፈጥሯል ሲል የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የከተማ አሰተዳደሩ አሸባሪውንና ወራሪው የህውሓት ቡድን እና ግብር አበሮቹ በከተማዋ የጥፋት ተልዕኮ እንዳይፈፅሙ በሁሉም የከተማዋ ክፍለ ከተሞች ህዝባዊ አደረጃጀት ተፈጥሮ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ገልፀዋል።

በግንባር ሂዶ የጠላትን ሀይል መዋጋት እንዳለ ሁኖ ቀሪው የከተማው ማህበረሰብ የጥፋት ሀይሎችን እኩይ ተግባር በመከላከል ረገድ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ሀላፊው ተናግረዋል።

በርካታ የፖሊስ አባላት ወደ ግንባር መዝመታቸውን የተናገሩት ኮማንደር አየልኝ ታክሎ፥ ቀሪዎቹ የፀጥታ አካላት የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ በኩል ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን አመልክተዋል።

የተፈጠረው ህዝባዊ አደረጃጀት ከአሁኑ ለውጦችን እያመጣ ነው ያሉት ሀላፊው ህዝቡም በንቃት በመሳተፍ ወቅታዊውን የሰላም ስጋት ለመቀልበስ በትጋት እየሰሩ ነው ብለዋል።

አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፥ አሸባሪው የህውሃት ቡድንና በተግባር የሚመስሉት ተላላኪዎች የጥፋት ሀይሎች ሁከትና አለመረጋጋት በከተማዋ እንዳይፈጥሩ ተገቢውን የአደረጃጀት ክትትል እያደረጉ ናቸው።

ሰርጎ ገቦች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡም ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት ተግባሮችን እየመሩ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የከተማው ፖሊስ መምሪያም የኢትዮጵያ ጠላቶች ከምድረገፅ እስኩጠፉ ድረስ የከተማው ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

በሰላም አስመላሽ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!