Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ጥቅምት 27 ቀን ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ምክንያቶች የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም መራዘሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
 
የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በ11ዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለተከታታይ 3 ቀናት አስመዝግበዋል፡፡
 
ሰዎች የማስመዝገብ ፍላጎቱ እያላቸው የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ፣ያላቸውን የጦር መሳሪያ ሌላ ቦታ በማስቀመጣቸው እና ማስመዝገብ እንደሚቻል በቂ መረጃ ያልሰሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡
 
ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
የጦር መሳሪያ የማያስመዘገቡ ግለሰቦች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆኑ እና የጦር መሣሪያው ለመንግስት ገቢ እንደሚደረግም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.