የህወሓት እና ሸኔ አገር የማፍረስ ሴራ እንደማይሳካ የጅማ ነዋሪዎች ገለጹ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሰልፍ በጅማ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በሰላማዊ ሰልፉ የሽብር ቡድኖቹን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዙ እና የህልውና ዘመቻውን የሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ሠልፈኞቹ የወያኔ አሽከር ሆኖ የሚያገለግለው ሸኔ እና ጨፍጫፊውና ዘራፊው ወያኔ የሚያካሂዱት አገርና ህዝብን የማጥፋት ሴራ እኛ በህይወት እያለን ሊሳካ አይችልም፣ የክተት ጥሪውን ተቀብለን በመዝመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እናስከብራለን ብለዋል።
ታጋሽና ሰላማዊ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ኢትዮጵያ ጠል የሆነውን የባዕዳን ተልዕኮ ለማስፈጸም እያካሄዱ ያለውን እንቅስቃሴ በጥብቅ እንደሚያወግዘው ሠልፈኞቹ ገልጸዋል።
በሙከታር ጠሃ እና ተመስገን አለባቸው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!