Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የአንበጣ መንጋ ዳግም ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ ዳግም መታየቱን የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የፀረ ተባዮች ዳይሬክተር አቶ መብራህቶም ገብረኪዳን የአንበጣ መንጋው ከዓርብ ምሽት ጀምሮ ከአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ወደ ክልሉ ደቡባዊ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች መግባቱን ተናግረዋል።

የአንበጣ መንጋው በመስኖ በለሙ ሰብሎችና በእንስሳት መኖ እንዲሁም ዛፎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የሚያመላክት መረጃ ለሁሉም የማዳረስ ስራ እንደተሰራም ጠቅሰዋል።

መንጋው ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመከላከል እና ከአካባቢው ለማጥፋት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

የአንበጣ መንጋውን በአጭር ጊዜ ለማጥፋትም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ ቀደም ያሳየውን የተቀናጀ ተሳትፎ በመድገም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.