በመላ ኦሮሚያ የወያኔንና የሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ በማውገዝ ሰላማዊ ሠልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላ ኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ሽብርተኞቹ ወያኔና ሸኔ ኢትዮጵያያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለማጥፋት እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ ተካሄደ።
ሠልፈኞቹ የወያኔ አሽከር ሆኖ የሚያገለግለው ሸኔ እና ጨፍጫፊውና ዘራፊው ወያኔ የሚያካሂዱት አገርና ህዝብን የማጥፋት ሴራ እኛ በህይወት እያለን ሊሳካ አይችልም፥ የክተት ጥሪውን ተቀብለን በመዝመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እናስከብራለን ብለዋል።
በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ባደረሱን መረጃ መሠረት፥ ታጋሽና ሰላማዊ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ኢትዮጵያ – ጠል የሆነውን የባዕዳን ተልዕኮ ለማስፈጸም እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በጥብቅ እንደሚያወግዙ ሠልፈኞቹ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከልም “ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት፣ እኔ እያለሁ ወያኔ ዳግም በህዝባችን ትከሻ ላይ የጭቆና ቀንበር አትጭንም፣ ወያኔን ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው፣ አልረሳም! ወያኔ የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ ጠላት ናት፣ እዘምታለሁ! የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብራለሁ፣ በአንድ እጃችን ልማታችንን ለማፋጠን፣ በሌላ እጃችን ጠላቶቻችንን ለመቅበር ተግተን እሠራለን! “ የሚሉ ይገኝበታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!